እረጂም ሳቅ
ሳሙኤል በለጠ (ባማ) ....ቀዘበዘኝ...ሒወት ካሉት ፍሪጅ ይሞቃል...ተብሎ ተተረተብኝ..ደስ የሚል ደስ የማይል ነገር አሳለፍኩ የቀቢጸ ተስፋ ነዶ ከምሬ(ነበር).... እውነት....ሐብናን ወደኔ ካልመጣች /..የተደፋብኝ ሰማይ/ የማረገው ነገር በደመ ነፍስ ይሆናል ማታ ስተኛ የቀዘቀዘ ትራስ አቅፋለሁ ትንሽ በመናፈቅ በስሜት እሰቃያለሁ እግሬን ከብርድ ልብሴ አወጣውና ንፋስ አስመታዋለሁ በሰማይ የተነሰነሱትን ርካሽ ሳንቲሞች በአይኖቼ እለቅማለሁ የበገና መዝሙር....ስሰማ እጸጸታለሁ የቅኝት ክሬ የተሰራው ከጸጸት ነው.. *የሚነታረኩ አባትና ልጅ አሉ ደሞ ጫማ ብሎ ንፍርቅ ብሎ አለቀሰ አረ ተው አንተ ልጅ ከዛፍ ላይ አይሸመጠጥ(ነዋይ) ታዲያ ለምን ባንኮች ቅርንጫፍ ኖራቸው ./ሸምጥጣ/ ሸምጥጥ ጺጺሮ...ይሉታል አልቃሻ ስለሆነ /ጅረት ንፍጥ ስላለው/ ..ቁርስ ይበላል ምሳ ይበላል ማታ ተረት ይበላል ተረት ተረት አንድ ሐብታም ነበረ እእሺ እና ያ ሐብታም እሺ.... ልጁ ደበረው ሳክስ አስጠላው ሐብናን...ራቀች ረቀቀች ሐብናን የምሽት ጸጌ ሬዳ አበባ ሆነች ... እናቴ (ሮሚ) በኔ ግራ ተጋባች...ተጭዋች ነበርኩ ዛሬ ዝም አልኩ እንደ ቀረሚላ ይጥም የነበረው አንደበት ተለጎመ(ርጭታ) ምነው ልጄ? አሳብ ገባህ? ተጨነክኮ? ለኔ ግን ደስ የሚል ስቃይ ነው የሆነብኝ ግራጫማ ነገር መሄድ መምጣት መምጣት መሄድ ብቻ.....እንደዚህ ነው.... ዳቢሎስና ሰይጣን.....እየተዋያዩ መሰለኝ.... ሰይጣን አደርገዋለሁ... ዳቢሎስ በደንብ አረገዋለሁ ሰይጣን ይቃጠላታል ዳቢሎስ በስሜት ይንበለበላታል..... እግዜር በፍቅር ነው?..... /ከሐሳቡ እንደ መንቃት ብሎ/ በፍቅር...ሃሃሃሃ አመጣም ዴ የከንፈር ወዳጅህ ብላ ...