እረጂም ሳቅ


ሳሙኤል በለጠ (ባማ)
....ቀዘበዘኝ...ሒወት ካሉት ፍሪጅ ይሞቃል...ተብሎ ተተረተብኝ..ደስ የሚል ደስ የማይል ነገር አሳለፍኩ የቀቢጸ ተስፋ ነዶ ከምሬ(ነበር)....
እውነት....ሐብናን ወደኔ ካልመጣች
/..የተደፋብኝ ሰማይ/
የማረገው ነገር በደመ ነፍስ ይሆናል
ማታ ስተኛ የቀዘቀዘ ትራስ አቅፋለሁ
ትንሽ በመናፈቅ በስሜት እሰቃያለሁ
እግሬን ከብርድ ልብሴ አወጣውና
ንፋስ አስመታዋለሁ
በሰማይ የተነሰነሱትን ርካሽ ሳንቲሞች በአይኖቼ እለቅማለሁ
የበገና መዝሙር....ስሰማ እጸጸታለሁ
የቅኝት ክሬ የተሰራው ከጸጸት ነው..
*የሚነታረኩ አባትና ልጅ አሉ ደሞ
ጫማ ብሎ ንፍርቅ ብሎ አለቀሰ
አረ ተው አንተ ልጅ ከዛፍ ላይ አይሸመጠጥ(ነዋይ)
ታዲያ ለምን ባንኮች ቅርንጫፍ ኖራቸው
./ሸምጥጣ/ ሸምጥጥ
ጺጺሮ...ይሉታል አልቃሻ ስለሆነ
/ጅረት ንፍጥ ስላለው/
..ቁርስ ይበላል ምሳ ይበላል ማታ ተረት ይበላል
ተረት ተረት አንድ ሐብታም ነበረ
እእሺ
እና ያ ሐብታም
እሺ....
ልጁ ደበረው ሳክስ አስጠላው
ሐብናን...ራቀች ረቀቀች ሐብናን የምሽት ጸጌ ሬዳ አበባ ሆነች ...
እናቴ(ሮሚ) በኔ ግራ ተጋባች...ተጭዋች ነበርኩ ዛሬ ዝም አልኩ እንደ ቀረሚላ ይጥም የነበረው አንደበት ተለጎመ(ርጭታ)
ምነው ልጄ?
አሳብ ገባህ?
ተጨነክኮ?
ለኔ ግን ደስ የሚል ስቃይ ነው የሆነብኝ
ግራጫማ ነገር
መሄድ መምጣት
መምጣት መሄድ
ብቻ.....እንደዚህ ነው....
ዳቢሎስና ሰይጣን.....እየተዋያዩ መሰለኝ....
ሰይጣን አደርገዋለሁ...
ዳቢሎስ በደንብ አረገዋለሁ
ሰይጣን ይቃጠላታል
ዳቢሎስ በስሜት ይንበለበላታል.....
እግዜር በፍቅር ነው?.....
/ከሐሳቡ እንደ መንቃት ብሎ/
በፍቅር...ሃሃሃሃ
አመጣም ዴ የከንፈር ወዳጅህ ብላ ጠየቀችኝ ሮሚ-
ዝም
ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ ተብሎ አልነበር
ዝም....
እሺሺሺሺ
ጥርጥር ምንጥር ምንቅር ምንቅር ቅር
...ከፊቴ እየቀደመች እብድ
..ንክት ንክትክት ባልንጋ ጣቷ
I hav to be romantic. ....1
እያለች በሯንዳ ድልድይ ወክ እያረግን ነበርኮ....
Mess ነው ሁሉ ነገር ጸጉሬን አልታጠብኩ(ላሳይህ)
እሺ......ቀላል አልኩ
(አልፎ....የሆነ ቀውጢ ቀን ላምበረት እንዳትቀር አለችኝ ሐብናን(በቴሌግራም)
ቀረሁ ቀረሁ በዛው
ከዛ ጊዜ ጀምሮ ዝዝዝዝዝዝዝዝዝ ሆነ ሒወቴ

Comments

Popular posts from this blog

ተስፋ ማድረግ ማለት (የተስፋ ግንድ የተስፋ መቁረጥ ፍሬ አፈራ) ሳሙኤል በለጠ(ባማ) *ከዕልታት አንድ ቀን ለብዙ ዓመታት ከሚያፈቅራት በመነጠሉ የሚያላዝን(የሚያቃትት)ና በብቸኝነት እሳት ውስጥ የተዋጠ አንድ እፍቃሪ ነበር፡፡ ከፍቅር ሕግጋት ውስጥ ትእግስት ከልቡ ተሟጠጠ ሥጋዊ አካሉም መንፈስ አልባ ሆነ ከእርሷ ውጪ ሕይወት ፌዝ መሆኑንን አወቀ ጊዜም እርሱን በልቶ ጨረሳው፡፡ እርሷን ለማግኘት መመኘት ብዙ ቀናት እረፍት ዐልባ ሆኖ ቆየ! ብዙ ለሊቶችም የእርሷን በማጠት ህመም እንቅልፍ አልባ አደረገው! ሥጋዊ አካሉ በናፍቆት ማቃሰት ነተበ የልቡ ቁስለት ወደ መሪር አልቃሽነት ቀየረው፡፡ የእርሷን ማገኘት ጽዋ አንድ ጊዜ ለመቅመስ ብቻ ሺህ ሕይወትን ይሰጣል ይህንን አድርጎ ግን አይበቃውም...ሐኪሞች የፈውስ መድሃኒት አላገኙለትም እናም ወዳጆች እርሱን ከመወዳጀት ተገለሉ አዎን የተወዳጁ ችሮታ ነጻ ካላወጣው በስተቀር ሐኪሞች በፍቅር ለታመመ ፈውስ የላቸውም፡፡ በመጨረሻም የብርቱ መሻቱ ዛፍ የተሰፋ መቁረጥ ፍሬ አፈራ የተስፋው እሳትም አመድ ሆነ፡፡ አንድ ቀን ምሽት ላይ ከዚህ በላይ መኖር አቃተው ከቤቱ ወጣና ወደ ከተማ ገበያ ቦታ ሄደ፡፡ በደንገትም አንድ ፖሊስ ይከታተለው ጀመር መሮጥ ጀመረ ፖሊሱም ተከተለው ሌላ ፖሊስም መጣና አበሮት መከተል ጀመሩ አቅጣጫዎቹን ሁሉ ዘጉበት፡፡ ምስጊኑ(አፍቃሪው) ከልቡ አለቀሰ በየአቅጣቸው መሮጥ ጀመረ ለራሱም እንዲህ ሲል አላዘነ “ በእርግጥ እነዚህ ፖሊሶች መልዐከ ሞት ናቸው በፍጥነትም እየተከታተሉኝ ነው። ወይም ደግሞ ሊጎዱኝ የፈለጉ ጨቃኝ ሰዎች ናቸው” ከዛም በግንብ አጥር የተከለለ መናፈሻ ቦታ ጋር ደረስ በጣም ረጅም አጥር ስለ ነበር እጅግ እየተሰቃየ አጠሩን ተወጣጣና በደመ-ነፍስም ወደ ታች ወደ መናፈሻው ተወረወረ፡፡ እዛም የእርሱ ተፈቃሪዋ በእጇ ማሾ ይዛ የጠፋባትን ቀለበት ስትፈልግ አያት፡፡ ይህ ልቡን ፈጽሞ አስረክቦ የነበረ አፍቃሪ የእርሱን የማትጠገብ ፍቅረኛውን ሲመለከት ትንፋሹን ወደ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ ሳበና እጁን ወደ ላይ በማንሳት በፀሎት ጮኽ “አምላኬ ሆይ! ክብርን ሃብትን ለፖሊሱ ስጠው፡፡ ምክንያቱ ድሃውን ሰው የማረ ጠባቂ ገብርኤል ነውና ወይንም ይኽንን የተገፋውን ሰው ህይወት የዘራለት..... በዚህ ጨካኝ በመሰለ ሁኔታ ውስጥ ሚስጥራዊ ሥውር ፍትሕ ስላገኘና እንዲሁም ከመጋራጃው በስተኋላ ብዙ የተሠወሩ ምህረቶች ሰላሉ በእውነት የእርሱ ቃላቶች እውነት ነበሩ፡፡ ፖሊሱ በቁጣ ተሞልቶ በፍቅር በረሃ ጥም ላይ ያለውን አፍቃሪ ወደ ፍቅረኛው ባህር መራው እንዲሁም የመራራቅን ድቅድቅ ጨለማ በእንደገና የመገናኘት ብርሃን አበራው በጣም ርቆ የነበረውን ሰው ወደ ቅርበት የአትክልት ሥፍራ አመጣው ታማ የነበረችውን ነፍስ ወደ ሐኪሙ ልብ መራት፡፡ አፍቃሪው አርቆ የማየት ችሎታ ቢኖረው ኖሮ ፖሊሱን ከመጀመርያው ባመሰገነና ለእርሱም ፀሎት ባደረገለት እንዲሁም ጭካኔውን እንደ ፍትሕ አድርጎ በተመለከተ ነበር ነገር ግን መጨረሻው ከእርሱ የተሰወረ በመሆኑ መጀመሪያ ላይ አለቀሰ አቤቱታም አቀረበ ነገር ግን እነዛ በእውቀት አትክልት ሥፍራ ላይ በመጓዝ ላይ ያሉ መጨረሻውን በመጀመርያ ላይ ስለሚያዩት በጦርነት ውስጥ ሰላም በኩርፊያ ውስጥ ጓደኝነትን ያያሉ፡፡ አበቃ! 2..... መንታ መንገድ በሁሉም ቦታ አለ የልቡናችንን በር ለማንኳኳት ስንደረደር በመንታ መንገዶች እንፈተናለን አቅጣጫ እንስታለን....(አንዱ መንገድ ስህተት ሌላው መንገድ ትክክል ወንም ሁለቱም ስህተት ሊሆን ይችላል) መንገዱስ እሺ ትክክል ነው እንበል እግሩ ቢሳሳትስ? *የዕውቀት በር እንበለው(አንድም ተስፋ)

አፍሮዳይት