Posts

Showing posts from November, 2021

አፍሮዳይት

 ሳሙኤል በለጠ(ባማ) የነፍስን ቅርጽ እያሰበ ቁዛሜውን ቀጠለ ክብ ፣ አራት ማዕዘን ፣ ሞላላ ፣ አባጣ ፣ ጎባጣ  ምንድናት ? አለ  እስከዛሬ ቀሚሳቸውን ገልቦ ላባቸው ላይ በልቡ የተንሳፈፈባቸውን ሴቶች አሰበ ፥ አሃ እንደውም ወንድ ነፍስ የለውም የሚል ክብ ሐሳብ ሠራ በክብቦሹ ይጦዛል ። የጥዋት ፀሐይ ማንም ሳያያት ከተቀመጠበት ዲንጋይ ሥር ፈቀቅ ብላ ተቀምጣለች የብርሐኗን ጨረር ስታሰፋው ወደ ሠማይ ራቀች ፥ ትላንት ሥዕል ሊስል ቢቀመጥ ሸራው ከፊት ምስሏ ከኋላ ሆነበት ፥ አማተበ እንዴት በፍቅረኛሞች መኃል መጋረጃ ሊኖር ቻለ? ሊያውም ፊትና ኋላ አለ ። የምናብ ዓለሙን እያስታወሰ እንዴት ይቀፋል ? አለ። እውቀት አንድ ነጥብ አለው ። አለማወቅ የተዘበራረቀ ነጥብ ነው ። ከተወላገደ ካካሉ ቀጥ ያለች ነፍሱን ለመፈለግ የቀለሞችን ነጥብ ማወቅ ፈለገ ግን ወንድ ውስጥ ነፍስ የለም ብሏል ፥ መንፈሳዊ ዓለሙን ሳይዳስስ ዓለማዊ ሕይወት ውስጥ ተደነቀረ ፥ ከጥላው ኋላ የምትከተለው ቅርጽ ዐልባዋን ነፍሱን እንዳይደፈጥጣት ፣ እንዳደፈጥጠው ይሳቀቃል ። ይፈልጋታል የእኔ ገነት እኔን ፣ ልቤን ፣ ቀለሜን ፣ እምነቴን ይዛለች ግን እኒህ በነፍስ ነው ። 'ሚታቀፉት አለው ራሱ ለራሱ ፥ ይህ ቡናማ ሐሳብ የልቡን አቶም ሰነጠቀው ፤ ሐሳቡ ሲሰክን ከስንጣቄው በጨለማ የተለወሰ ብርሐን ወጣ ፥  ከሚስለው ሥዕል ቀድሞ የፍትወት ቅርጽ አዕምሮው ላይ ይመጣል ፤ ገላዋ ሲነቃነቅ ቡርሹ ቀለም ይጠጣና በተንጋደደ ሸራው ላይ እግሯን ያጋድመዋል የእግር ጌጥ ይጨምርበታል ። ወዲያው ወደ ጉልበቷ ይሮጣል ። አጠፍ ያደርገውና ያዝለፈልፈዋል ። ፊቷ ወደ ማያየው ጀርባዋን መደሚያየው አድርጎ ይስላታል ። በባህር ውስጥ ደረቅ አድርጎ ፣ በብርሐን ውስጥ ጨለማ አድርጎ ፣ በውኃ ው...